የፎረንሲክ ህክምና ምርመራ ፕሮግራሞች
1-844-443-5732
www.dcsane.org
የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ለጾታዊ ጥቃት፣ ለቅርብ አጋር ጥቃት፣ ወይም ለጾታዊ ግንኙነት ተጎጅዎች ሁለት የፎረንሲክ ህክምና ፕሮግራሞችን ይሰጣል።
የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የጾታዊ ጥቃት ነርስ መርማሪ (DC SANE) ፕሮግራም የከንቲባው ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ፣ የተጎጅ አገልግሎቶች ቢሮ፣ ሜድስታር ዋሽንግተን ሆስፒታል ሴንተር፣ የዲሲ የፎረንሲክ ነርስ መርማሪዎች ቢሮ እና የዲሲ የተጎጂ ማገገሚያ ኔትዎርክ ጥምረት ነው። የዲሲ ሴን (SANE) ፕሮግራም የአስገድዶ መድፈር፣ የጾታዊ ጥቃት፣ እና ሌሎች ወሲብን የሚመለከቱ ወንጀል ሰለባ ለሆኑ አዋቂ እና ወጣቶች አጠቃላይ የሆነ የህክምና፣ የፎረንሲክ እና የጥብቅና እንክብካቤ ይሰጣል።
የዲሲ የፎረንሲክ ነርስ መርማሪ የቅርብ ጾታዊ አጋር ጥቃት ፕሮግራም የዲሲ የፎረንሲክ ነርስ መርማሪዎች (DCFNE) እና ከጉዳት የተረፉ እና የአቅም ግንባታ ጠበቆች (SAFE, Inc.) የጋራ ጥምረት ነው። የDCFNE የቅርብ ጾታዊ አጋር ጥቃት (IPV) ፕሮግራም አጠቃላይ የህክምና፣ የፎረንሲክ እና የጥብቅና እንክብካቤን ለአዋቂና ለወጣቶች የቅርብ ጾታዊ አጋር ጥቃት፣ የጾታዊ ግንኙነት ጥቃት፣ ወይም የቤት ውስጥ ጥቃት ተጎጅዎች ይሰጣል።
ዲሲ ሴን (SANE) እና DCFNE IPV ፕሮግራም የድንገተኛ ህክምና ፎረንሲክ ምርመራዎችን፣ የአዕምሮ ጤና ወደሌላ መምራትን፣ የኤች አይ ቪ ምርመራዎችን፣ የፕሮፊላክሲሲ መድሃኒት (አስፈላጊ ሲሆን) እና ማጠቃለያ የጥብቅና አገልግሎቶች በነጻ ይሰጣል። ከጉዳት የተረፈ ሰው ክስተቱን ለፖሊስ ሪፖርት ቢያደርግም ባያደርግም እነዚህን አገልግሎቶች ማግኘት ይችላል።
ከላይ ካሉት አንዱን ምርመራ ለማግኘት እርስዎ ወደ ሜድስታር ዋሽንግተን ሆስፒታል ሴንተር የድንገተኛ ክፍል በመምጣት የፎረንሲክ ምርመራ መጠየቅ ይችላሉ ወይም ወደ ሆስፒታሉ ነጻ መጓጓዣ ለማመቻቸት በ1-844-443-5732ይደውሉ።
ሁለቱም የዲሲ ሴን (SANE) እና DCFNE IPV የምርመራ አገልግሎቶች የሚከተሉቱን ሊያካትቱ ይችላሉ፣
- አጠቃላይ የአካል ምርመራ
- መረጃ መሰብሰብ
- የፎረንሲክ ዲጅታል ፎቶግራፍ
- የጉዳት መረጃ ማጠናከር
- የቅድመ መከላከያ መድሀኒቶች
- ምርመራ እና የፕሮፊላክቲክ በግብረስጋ ግንኙነት ተላላፊ ለሆኑ በሽታዎች(STIs)/ ኤች አይ ቪ እና እርግዝና ህክምና
- የችግር ምክር፣ ጥብቅና እና ኬዝ ማኔጅመንት
- ሌሎች የማህበረሰብ መምሪያዎች
ሜድስታር ዋሽንግተን ሆስፒታል ሴንተር ከሁለቱም ወንጀሎች ለተረፉ የህክምና አስተርጓሚዎችን ሊያቀርብ ይችላል።