ሜድስታር ዋሽንግተን ሆስፒታል ሴንተር

MedStar Washington Hospital Center

ሜድስታር ዋሽንግተን ሆስፒታል ሴንተር ለወሲብ ጥቃት እና የጾታዊ ግንኙነት ወይም የቅርብ አጋር ጥቃት ሰለባዎች በቀን 24 ሰዓት ሳምንቱን በሙሉ የፎረንሲክ ህክምና ምርመራ ይሰጣል። ምርመራው ተጎጅው እንደሚፈልገው ይደረጋል፣ ሆኖም ማስረጃ ማሰባሰብን፣ አጠቃላይ የህክምና ምርመራን፣ ቅድመ መከላከል ህክምናዎችን እና ዘላቂነት ወደ አላቸው የመረጃ ቦታዎች መምራትን ሊያካትት ይችላል። እዛው ሆስፒታል ውስጥ እያሉ ክስተቱን ሪፖርት በማድረግ ፖሊስ ማናገርን ሊመርጡ ይችላሉ፣ ነገር ግን ዝግጁ እስኪሆኑ ድረስ ለፖሊስ ወይም ለማንኛውም ሰው መንገር አይኖርብዎትም። ሪፖርት ለማድረግ እስኪወስኑ ድረስ (እስከ 90 ቀናት) መረጃዎ ሊሰበሰብ እና በሚስጥራዊነት ሊያዝ ይችላል።

ወደ ሆስፒታል ነጻ የኡበር ታክሲ መጓጓዣ ለማግኘት በ1-844-443-5732 ይደውሉ እንዲሁም ሚስጥራዊ ጠበቃ በሆስፒታሉ ውስጥ እንዲያገኙ መልዕክት ያስተላልፉ።

 

አፑን ያግኙ

በኮሎምቢያ ዲስትሪክት የጾታዊ ጥቃት ቢደርሰብዎት ወዲያውኑ በጣም ተፈላጊ የሆነውን መረጃ ያግኙ--በፍጥነት፣ በሚስጥራዊ፣ እና በነጻ። ይህ በጣም አስፈላጊ መሳሪያ ለማንኛውም ዲሲ ለሚኖር ወይም ዲሲን ለሚጎበኝ ነው። ከዚህ በታች ከተመለከቱት አንዱን ሊንክ ይጫኑ ወይም “አስክ ዲሲ”ን በአይቱይንስ አፕ መደብር፣ ጉግል ፕሌይ መደብር፣ ወይም በብላክቤሪ አፕወርልድ ይፈልጉ።

icon_app_store icon_google_play