
ሜድስታር ዋሽንግተን ሆስፒታል ሴንተር ለወሲብ ጥቃት እና የጾታዊ ግንኙነት ወይም የቅርብ አጋር ጥቃት ሰለባዎች በቀን 24 ሰዓት ሳምንቱን በሙሉ የፎረንሲክ ህክምና ምርመራ ይሰጣል። ምርመራው ተጎጅው እንደሚፈልገው ይደረጋል፣ ሆኖም ማስረጃ ማሰባሰብን፣ አጠቃላይ የህክምና ምርመራን፣ ቅድመ መከላከል ህክምናዎችን እና ዘላቂነት ወደ አላቸው የመረጃ ቦታዎች መምራትን ሊያካትት ይችላል። እዛው ሆስፒታል ውስጥ እያሉ ክስተቱን ሪፖርት በማድረግ ፖሊስ ማናገርን ሊመርጡ ይችላሉ፣ ነገር ግን ዝግጁ እስኪሆኑ ድረስ ለፖሊስ ወይም ለማንኛውም ሰው መንገር አይኖርብዎትም። ሪፖርት ለማድረግ እስኪወስኑ ድረስ (እስከ 90 ቀናት) መረጃዎ ሊሰበሰብ እና በሚስጥራዊነት ሊያዝ ይችላል።
ወደ ሆስፒታል ነጻ የኡበር ታክሲ መጓጓዣ ለማግኘት በ1-844-443-5732 ይደውሉ እንዲሁም ሚስጥራዊ ተቆርቋሪ በሆስፒታሉ ውስጥ እንዲያገኙ መልዕክት ያስተላልፉ።