• በከተማው ውስጥ እርዳታ ያግኙ

  • ተጨማሪ ግልጋሎቶች

  • ተመልሶ መግቢያ

ኮምዩኒቲ ፋሚሊ ላይፍ ሰርቪስስ (Community Family Life Services)

  • ኮምዩኒቲ ፋሚሊ ላይፍ ሰርቪስስ ቤት አልባ አዋቂዎች፣ ቤተሰቦች እና ተመላሽ ዜጋ ለሆኑ ሴቶች ከቤተሰቦቻቸው ጋር በድጋሚ እንዲገናኙ እና በተሟላ አቅማቸውን ሕይወታቸውን እንዲኖሩ መሳሪያዎችን እና ድጋፍ የሚያቀርብ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው።  የእነሱ ፕሮግራም እና አገልግሎቶች የሚያካትቱት፡ ጊዜያዊ መኖሪያ ቤት፣ ከእስር መፈታት በኋላ ቤታቸው ለሚመለሱ ሴቶች ማማከር፣ የሥራ ቅጥር ድጋፍ፣ የክስ መዝገብ አስተዳደር፣ የቤተሰብ ትምህርት፣ እና እንደ ምግብ እና የልብስ ማስተዳደር የመሳሰሉ ድንገተኛ አገልግሎቶች መስጠት ነው። 

  • ዋና

    202-347-0511

  • አድራሻ

    305 E Street NW, Washington, DC 20001

  • ድህረ ገጽ

    http://www.cflsdc.org

ትራይቭ ዲሲ (Thrive DC)

  • ትራይቭ ዲሲ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ሕይወታቸውን እንዲያረጋጉ ለማገዝ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን በማቅረብ በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ጎዳና ተዳዳሪነትን ለመከላከል እና ለማቆም ይሰራል። ዘ ውመን ኢን ኒው ዳይሬክሽንስ (WIND) በድጋሚ መመዝገቢያ ፕሮግራም የተዘጋጀው በቅርብ እስር ቤት የገቡ እና/ወይም የተለቀቁ ሴቶችን ለማገዝ፣ ከእስስ ቤት ሕይወት መልስ የተሳካ ሕይወት እንዲኖራቸው ነው። አገልግሎቶች የሚያካትቱት:

    • የክስ መዝገብ ማስተዳደር
    • መሰረታዊ ነገሮች ድጋፍ (ምግብ፣ መፀዳጃዎች፣ አልባሳት፣ የኪስ ገንዘብ)
    • የትራንስፖርት ድጋፍ
    • የህይወት ክህሎቶች ትምህርት
    • ከአልኮል ነፃ መሆን እገዛ እና ድጋፍ
    • የቅጥር ድጋፍ

  • ዋና

    202-737-9311

  • አድራሻ

    1525 Newton St NW Washington, DC 20010

  • ድህረ ገጽ

    https://www.thrivedc.org