• ለሆነ ሰው ያናግሩ

  • ለሆነ ሰው ያናግሩ

የዲሲ የአስገድዶ መድፈር ችግር ማዕከል

  • የዲሲ የአስገድዶ መድፈር የችግር ማዕከል ከጉዳት ለተረፉ እና በርካታ ለሆኑ ሌሎችም (ቤተሰብ፣ ጓደኞች፣ እና አጋሮች) ነጻ የምክር አገልግሎት ይሰጣል። የዲሲ የአስገድዶ መድፈር ችግር ማዕከል የምክር አገልግሎት ሞዴል
    ሰዎች የራሳቸውን የተፈጥሮ ጥበብ እና እውቀትን ተጠቅመው ጉዳታቸውን እንዲያድኑ በሚያበረታታ ሞዴል ላይ የተመሠረተ ነው። የዲሲ የአስገድዶ መድፈር ችግር ማዕከል ቲራፒስቶች በደንበኞቻቸው ህይወት ረዳቶች እንጂ መሪዎች አይደሉም። ክፍለ ጊዚያቶቹም ከጉዳት የተረፉ በህይወታቸው ማድረግ በሚፈልጉት ነገር ላይ የተመሠረቱ ይሆናሉ።

     

  • የማማከር

    202-232-0789

  • አድራሻ

    5321 First Place NE Washington, DC 20011

  • ድህረ ገጽ

    www.dcrapecrisiscenter.org

የብሔራዊ ጾታዊ ጥቃት ሆትላይን

  • የአስገድዶ መድፈር፣ ጥቃት እና የኢንሰስት ብሔራዊ ኔትዎርክ (RAINN) 24 ሰዓት በቀን ሳምንቱን በሙሉ የብሔራዊ የጾታ ጥቃት ሆትላይን በማንቀሳቀስ ነጻ፣ ሚስጥራዊ እና ማንነትን ሳያሳውቅ ምክር ይሰጣል። በተጨማሪም RAINN ከጾታዊ ጥቃት ለተረፉ ሰዎች የውይይት አገልግሎት የሚሰጥ የብሔራዊ የጾታ ጥቃት ኦንላይን ሆትላይንን ያንቀሳቅሳል። RAINN ጾታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው የመከላከያ መምሪያ ማሕበረሰብ ዓባላት የመከላከያ መምሪያን የኦንላይ የእርዳታ መስመር እና የስልክ ሆትላይኖችን ይጠቀማል።

    የብሔራዊ የጾታ ጥቃት ሆትላይን፣ 1-800-656-4673

  • Hotline

    1-800-656-4673

  • ድህረ ገጽ

    www.rainn.org

ምርመራ ለማድረግ

  • ነፃ የኡበር ታክሲ አገልግሎት ወደ ሜድስታር ዋሽንግተን ሆስፒታል ማዕከል እንዲያገኙ እና በሆስፒታል ውስጥ በሚስጥር የእርስዎን ጉዳይ የሚከታተል ሰው እንዲመደብልዎ ወይም/እና የአባዲና ምርመራ ለማድረግ 24/7 ይደውሉ።

  • የዲሲ ተጠቂ ነፃ የስልክ ቁጥር

    1-844-443-5732

የዲሲ ሰለባዎች የስልክ መስመር

  • የዲሲ ሰለባዎች የስልክ መስመር ለሁሉም በዲስትሪክት ኦፍ ኮሎምቢያ የወንጀል ሰለባዎች ለ 24/7   ክፍት ነው። ኦንላይን ቻቱ የሚገኘው ከ  12ፒኤም - 5ፒኤም ሰ-አ ነው። የሰለባ ድጋፍ ባለሙያዎች በማህበረሰቡ ለሚገኙ ከስር እንደተጻፉት ያሉ የአካባቢ ድርጅቶች እና ደጋፊዎች መረጃ፣ ድጋፍ እና ማስተላለፍን ያቀርባል። : 

    • የወንጀል ሰለባዎች ካሳ ድጎማን ማግኘት 
    • የህክምና እና የማስረጃ ምርመራዎችን
    • የመኖሪያ ቤት ድጋፍን 
    • የህግ ድጋፍ
    • የአእምሮ ጤና ምክር እና የድጋፍ ቡድኖችን
    • እንዳስፈላጊነቱ ሌላ የግል እርዳታን 

  • የስልክ መስመር

    844-443-5732

  • ቲቲዋይ

    711

  • ድህረ ገጽ

    http://dcvictim.org

ስትሮንግሃርትስ የቀደምት አሜሪካዊን የእርዳታ መስመር

  • ስትሮንግሃርትስ ከቤት ውስጥ ጥቃት የተረፉ የአሜሪካ ቀደምት ነዋሪዎችን እና የሚመለከታቸው ቤተሰቦች እና ጓደኞችን ለማገልገል የተመሰረተ ከባህል አብሮ ጋር የሚሄድ፣ የማይታወቅ፣ ሚስጥራዊ አገልግሎት ነው። ከጉዳት ለተረፉ ሰዎች ደህንነት እንዲያገኙ እና ከጥቃት ነፃ የሆነ ሕይወት እንዲኖሩ የሚያስችል ሕይወት የሚያተርፍ መሳሪያዎችን እና ፈጣን ድጋፍ የሚሰጡ ከስትሮንግሃርትስ ዕውቀት ያላቸው ተሟጋቾች ጋር አንድ ለ አንድ ያለምንም ወጪ ደዋዮች ከሰኞ እስከ አርብ ከ ከጠዋቱ 9 ሰዓት እስከ ከምሳ በኋላ 5:30 ድረስ CST ላይ መገናኘት ይችላሉ። ከላይ ከተጠቀሰው ሰዓት ውጪ የሚደውሉ ደዎዩች ከብሔራዊ የቤት ውስጥ የጥቃት ነፃ የስልክ መስመር ጋር የመደወል፣ ወይም በሚቀጥለው የሥራ ቀን የመደወል አማራጭ አላቸው።

  • የእገዛ መስመሮች

    1-844-762-8483

  • ድህረ ገጽ

    http://www.strongheartshelpline.org/

ላቭ ኢዝ ሪስፔክት (Love is Respect)

  • ላቭ ኢዝ ሪስፔክት የፍቅር ቀን ቀጠሮ ጥቃት ለደረሰባቸው ለታዳጊ ልጆች እና ለወጣቶች እና ለጓደኞቻቸው እና ለቤተሰብ የተዘጋጀ የ 24/7 ነፃ የስልክ መስመር እና የመስመር ላይ የውይይት አገልግሎት ነው። አገልግሎቶቹ ነፃ እና ሚስጥራዊ ናቸው። ፍቅር መከባበር ነው ለብሔራዊ የቤት ውስጥ ጥቃት ነፃ የስልክ መስመር እና ብሬክ ዘሳይክል ፕሮጀክት አካል ነው።

  • የእገዛ መስመርን አክብሩ

    1-877-331-9474

  • TTY

    1-866-331-8453

  • ድህረ ገጽ

    http://www.loveisrespect.org

Take Back the Night Legal Advocacy Hotline