• በከተማው ውስጥ እርዳታ ያግኙ

  • እድሚያቸው ከ18 ዓመት በታች ለሆነ እና ወጣቶች አገልግሎቶች

አማራጭዎን ይጎብኙ ከ 18 በታች

  • ከ 18  በታች ሆነው እና አማራጭዎን በምስጢር ለማማከር ከፈለጉ፣ እባከዎትን የዲሲ መደፈር ቀውስ ማዕከል ጋር ይደውሉ።

    የዲሲ ተጠቂ ማገገሚያ ኔትወርክ (ኤንቪአርዲሲ) ቢሮ በተለመደው የስራ ሰዓታት በመደወል ስለአማራጭዎ ከሰለጠነ ተሙዋጋች ጋር ሰ-አ 9-5 ደውለው ያናግሩ።

  • ዲሲ መደፈር ቀውስ ማዕከል 24/7 የስልክ መስመር

    202-333-7273

  • NVRDC

    202-742-1720

የህክምና ወንጀል ነክ ምርመራዎች 12-17 እድሜ አመታት

  • የፍቅር ጓደኛ ጥቃት (አይፒቪ) / የፍቅር ግንኙነት ጥቃት አይፒቪ ምርመራዎች በ 24/7  ሲሰጡ የሚገኙትም በሜድስታር ዋሽንግተን ሆስፒታል ማእከል የድንገተኛ ዲፓርትመንት ነው። ምርመራዎች 12  እና ከዛ በላይ እድሜ ላላቸው ይሰጣል።

    ወሲባዊ ጥቃት ነርስ መርማሪ (ኤስኤኤንኢ) ፕሮግራም  ኤስኤኤንኢ ምርመራዎች በ 24/7  ሲሰጡ የሚገኙትም በሜድስታር ዋሽንግተን ሆስፒታል ማእከል የድንገተኛ ዲፓርትመንት ነው። ምርመራዎች 13  እና ከዛ በላይ እድሜ ላላቸው ይሰጣል።

    ሁለቱም ምርመራዎች የሚሰጡት ከክፍያ ነጻ በሆነ ሁኔታ ነው። የመድህን ዋስትና ማስረጃ አያስፈልግዎትም። የዜግነት ማስረጃ አያስፈልግዎትም። ጉዳዩ ወላጅ ወይም ተንከባካቢን ካላካተተ፣ የፖሊስ ሪፓርት አያስፈልግም።

    ወደ ሜድስታር ዋሽንግተን ሆስፒታል ማእከል ነጻ መጓጓዣ ለማግኘት፣1-800-641-4028 ይደውሉ። 

  • Transportation

    1-844-443-5732

የሜዲካል ፎረንዚክ ምርመራዎች (Medical Forensic Exams)

  • የፎረንዚክ የሜዲካል ምርመራዎች (Forensic Medical Examinations) – ከ0-17 ዕድሜ ያላቸው የፎረንዚክ የሜዲካል ምርመራዎች (Forensic Medical Examinations) ከ0-17 ዕድሜ ላላቸው፣ በልጆች ብሄራዊ የሕክምና ማዕከል - Children’s National Medical Center (CNMC) ይሰጣል፡፡  የፎረንዚክ የሜዲካል ምርመራ (Medical Forensic Exam) ለማግኘት ወይም ተከራካሪ ወኪል ከሆነ ሰው ጋር ለመነጋገር፣ እባክዎን ወደ CNMC ይደውሉ እና በስልክ የተወከለውን የሕክምና ባለሙያ (on-call clinician) ለማነጋገር ይጠይቁ፡፡   
     
    በስልክ የተወከለውን የሕክምና ባለሙያ (On-Call Clinician) ለማነጋገር፡ 202-476-4100 

  • በስልክ የሚጠራ ክሊኒሺያን

    202-476-4100

  • ድህረ ገጽ

    https://childrensnational.org/departments/child-and-adolescent-protection

ደህና ዳርቻዎች (Safe Shores)

  • ደህና ዳርቻዎች የልጆች ጠባቂዎች የሚባል ስልጠና ሲያቀርብ፣ ስልጠናው አዋቂዎች እንዴት የልጅ ወሲባዊ ጥቃትን መከላከል፣ ማስተዋል እና በሃላፊነት እርምጃ መውሰድ እንደሚቻል ግንዛቤ ለማስጨበጥ ያስተምራሉ። በተጨማሪም፣ የተከታታይ ጣልቃ ገብነት ስልጠና ያቀርባሉ።

  • ዋና መንገድ

    202-645-3200

  • አድራሻ

    429 O Street, NW Washington, DC 20001

  • ድህረ ገጽ

    http://www.safeshores.org/

  • ኢሜይል

    team@safeshores.org

የልጆች ብሄራዊ የህክምና ማዕከል፡ የልጅ እና የጎረምሳ ጥበቃ ማዕከል

  • የፍሬዲ ማክ ፋውንዴሽን የልጅ እና ጎረምሳ ጥበቃ ማዕከል ለልጅ ጥቃት ሰለባዎች እና ቤተሰቦቻቸው የሚረዱ የጤና ባለሙያዎች ቡድን ሲሆን በዲስትሪክ ኦፍ ኮሎምቢያ ብቸኛው የህክምና ማዕከል ነው። የማዕከሉ የጤና ባለሙያ ቡድኖች የተሙዋል ምርመራዎችን (በወንጀል ነክ ሁኔታዎች የተካኑ በህጻናት ሃኪሞች እና ነርሶች)፣ በወሲብ የሚተላለፉ በሽታዎች እና ጉዳቶች ህክምና፣ እና በሁሉም አይነት ጥቃቶች የተጎዱ የልጆች ተጠቂዎችን የጥቃት ምክር (በህጻናት ጥቃት እና ትንኮሳ ልዩ ብቃት ባላቸው በአእምሮ ህክምና ባለሙያዎች እና ክሊኒካል ሶሻል ወርከሮች) ያቀርባል።

    የማዕከሉ ሌሎች አገልግሎቶች የሚያጠቃልሉት፥ ለተጠቂዎች እና ቤተሰቦች መሙዋገት

    የስነ አእምሮ ምርመራ

    የጎረምሳ ወንጀለኛ ምክር አገልግሎቶች

    ትምህርታዊ፣ ስነ አእምሮአዊ፣ እድገታዊ፣ እና የወላጅ፡ህጻን ግንኙነት ምዘናዎች

    ግላዊ እና ቤተሰባዊ ቴራፒ ለተጠቁ ህጻናት  (እድሜያቸው 4-22 አመታት ለሆኑ ወንጀል ነክ ላልሆኑ የአእምሮ ጤና አገልግሎቶች)

    የወላጅነት ትምህርት ቴራፒ ትምህርቶች

    ጉዳይ አስተዳደር

    ለተጠቂዎች እና ቤተሰቦቻቸው የመምራት አገልግሎቶች

  • ዋና መስመር

    202-476-4100

  • ምሽቶች እና የሳምንቱ መጨረሻዎች

    202-476-5000

  • አድራሻ

    Children’s National, 111 Michigan Avenue, NW Washington, DC 20010

  • ድህረ ገጽ

    http://childrensnational.org/departments/child-and-adolescent-protection

ሪልቶክዲሲ

  • የሪልቶክዲሲ ቡድን እድሜያቸው ከ 13 እስከ 24 አመት የሆኑትን ወጣቶች ስለጾታዊ ጤና መረጃ፣ የስልጠና እድሎችን፣ ነጻ ኮንዶሞች፣ ኤችአይቪ/ኤስቲአይ/የእርግዝና ምርመራ እና ለራሳቸው ደህና ቦታን ያገናኛቸዋል።

    ሰአቶቹ ከሰኞ እስከ አርብ ከ 3:30 ፒኤም – 7 ፒኤም በትምህርት አመቱ እና ከ 1 ፒኤም – 7 ፒኤም በበጋ ወራት ነው። 

  • አድራሻ

    651 Pennsylvania Ave, SE Washington, DC 20003

  • ድህረ ገጽ

    http://www.realtalkdc.org/

ብሬክ ዘ ሳይክል (Break the Cycle)

  • ብሬክ ዘ ሳይክል በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በፍቅር ቀን ቀጠሮ ጥቃት፣ በቤት ውስጥ ጥቃት፣ ሰላም መነሳት፣ ወይም የወሲብ ጥቃት ለደረሰባቸው ዕድሚያቸው ከ 12-24 ለሆኑ ወጣት ከጥቃት የተረፉ ሰዎች ነፃ የሕግ ማማከር አገልግሎት ይሰጣል። የትርጉም አገልግሎት ይገኛል።

  • ዋና

    202-849-6289

  • ድህረ ገጽ

    www.breakthecycle.org

  • ኢሜይል

    mberesin@breakthecycle.org

ላቭ ኢዝ ሪስፔክት (Love is Respect)

  • ላቭ ኢዝ ሪስፔክት የፍቅር ቀን ቀጠሮ ጥቃት ለደረሰባቸው ለታዳጊ ልጆች እና ለወጣቶች እና ለጓደኞቻቸው እና ለቤተሰብ የተዘጋጀ የ 24/7 ነፃ የስልክ መስመር እና የመስመር ላይ የውይይት አገልግሎት ነው። አገልግሎቶቹ ነፃ እና ሚስጥራዊ ናቸው። ፍቅር መከባበር ነው ለብሔራዊ የቤት ውስጥ ጥቃት ነፃ የስልክ መስመር እና ብሬክ ዘሳይክል ፕሮጀክት አካል ነው።

  • የእገዛ መስመርን አክብሩ

    1-877-331-9474

  • TTY

    1-866-331-8453

  • ድህረ ገጽ

    http://www.loveisrespect.org