• በከተማው ውስጥ እርዳታ ያግኙ

  • የክትትል አገልግሎቶች

የዲሲ የአስገድዶ መድፈር ማዕከል አገልግሎቶች

  • የዲሲ አስገድዶ የመድፈር አደጋ ማዕከል (DCRCC) ከጾታዊ ጥቃት ነጻ የሆነ ዓለምን ለመፍጠር የሚተጋ ያለትርፍ የተቋቋመ ድርጅት እና በኮሎምቢያ ዲስትሪክት አስገድዶ የመድፈር አደጋ ማዕከልነት የተመረጠ ነው። DCRCC ማህበረስቡን በመድረስ፣ የትምህርት እና ህጋዊ የህዝብ ፖሊሲ ሀሳብ በማቅረብ ለማህበራዊ ለውጥ ይሠራል። ከጾታዊ ጥቃት በኋላ ከጉዳት የተረፉትን እና ቤተሰቦቻቸውን ጣልቃ በመግባት፣ በማማከር እና ጥብቅና በመቆም እንዲጽናኑ ይረዳል።

  • የማማከር

    202-232-0789

  • ሆትላይን

    202-333-7273

  • አድራሻ

    5321 First Place NE Washington, DC 20011

  • ድህረ ገጽ

    dcrapecrisiscenter.org

ዲሲ ጸረ ጥቃት ፕሮጀክት

  • ዲሲ ጸረ ጥቃት ፕሮጀክት (ዲሲኤቪፒ) ለኤልጂቢቲ ማህበረሰብ የሚሰራ የዲሲ ማዕከል ፕሮግራም ነው። ዲሲኤቪፒ የሚሰራው በሌዝቢያን፣ ጌይ፣ ባይሴክሹዋል፣ እና ትራንስጄንደር (ኤልጂቢቲ) ግለሰቦች ላይ የሚፈጸም ጥቃትን ለመቀነስ ነው— እናም ኤልጂቢቲ ተብለው የሚታሰቡትን—በዲስትሪክ ኦፍ ኮሎምቢያ ላሉት በማህበረሰብ መዳረስ፣ ማስተማር፣ እናም የኤልጂቢቲ ተጠቂዎች መብቶች እና ክብሮች እንዲጠበቁ ጉዳያቸውን በመቆጣጠር ይሰራል። 

    የዲሲ ማዕከል ለኤልጂቢቲ ማህበረሰብ የሚያቀርበው የአእምሮ ጤና ድጋፍን ሲሆን የግለሰብ እና የቡድን አገልግሎቶችን የሚከተሉትን አይነት ጥቃቶች ሰለባዎች ለሆኑት የኤልጂቢቲ ማህበረሰብ አባላትን ነው፤ የፍቅረኛ ጥቃቶችን (አይፒቪ)  የቤት ውስጥ ጥቃት፣ የወሲብ ጥቃት፣ የጥላቻ ወንጀሎችን፣ ትንኮሳን። የዲሲ ማዕከል የሶሻል ሰራተኛን ያግኙ፥ ሳም ሺንበርግ በ፥ samantha@thedccenter.org

  • ዋና መስመር

    202-682-2245

  • አድራሻ

    2000 14th Street NW Suite 105 Washington DC 20009

  • ድህረ ገጽ

    http://www.dcavp.org

ዌንድት የጉዳት እና ማገገሚያ የምክር አገልግሎት ማዕከል

  • ሳተላይት ቢሮ 2041 Martin Luther King Jr. Ave SE, Suite 239
    Washington, DC 20020

    የዌንድት ማዕከል ከልጆች፣ ታዳጊዎች እና አዋቂዎች በተናጠል፣ በቤተሰብ እና በድጋፍ ቡድኖች ሙያ እና ልምድ ያላቸው አማካሪዎችን ይሰጣል። አገልግሎቶቹ በአስደንጋጭ ጉዳት፣ የወንጀል ሰለባ እና ጥቃት ዙሪያ ልምድ እና ፈቃድ ባላቸው የክሊኒክ ሠራተኞች፣ የፕሮግራም ሠራተኞች እና በጥሞና በሰለጠኑ በጎ አድራጊዎች ይሰጣሉ። በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ የቅርብ ዘመድ ተገድሎባቸው በሀዘን ላይ ለሆኑ ወይም ከቤት ውስጥ ጥቃት፣ የህጻናት ጥቃት፣ የጾታዊ ጥቃት ወይም ከሌሎች ወንጀሎች ለተረፉ ማጽናናት፣ መረጃ እና አስፈላጊ እርዳታ እንሰጣለን። ተንከባካቢና ተቆርቋሪ ሠራተኞቻቸው የመፈወሻ መንገዶችን የሚያውቁ ሲሆኑ የባለሞያ ድጋፍና መመሪያ ይሰጣሉ። የማማከር አገልግሎትን በዋና ቢሯቸው በኖርዝ ዌስት ዋሽንግተን ዲሲ ወይም በሳተላይት ቢሮዎቻቸው በሳውዝ ኢስት እና በኖርዝ ዌስት ዋሽንግተን ይሰጣሉ።

  • ዋና መስመር

    202-624-0010

  • አድራሻ

    4201 Connecticut Avenue, Suite 300 Washington, DC 20008

  • ድህረ ገጽ

    www.wendtcenter.org

አስጊ ያልሆነ መኖሪያ ቤት የዲስትሪክት ጥምረት (DASH)

  • (DASH) የድንገተኛ እና የመሸጋገሪያ አስጊ ያልሆነ ቤት በችግር ሁኔታ ላይ ላሉ ሴቶች እና ልጆች ሊሰጥ ይችላል፣ በተጨማሪም አደገኛ የሆነ የቤት ለመልቀቅ ወይም ለመቀየር መረጃዎችን ሊሰጥ ይችላል። እነኝህ አገልግሎቶች ኮንትራትን ለመቀየር ወይም ለማቋረጥ፣ የቤት አድሎን ሲገጥም ምን ማድረግ እንደሚቻል የሚገልጹ መረጃዎች፣ አዲስ ቤት ለማግኘት የሚረዱ መረጃዎች እና ከገንዘብ እና ከቤት ጥገኝነት እንደገና ለመላቀቅ የሚረዳ እገዛን ያካትታል።

  • ዋና መስመር

    202-742-1728

  • አድራሻ

    P.O. Box 91730 Washington, DC 20090

  • ድህረ ገጽ

    www.dashdc.org

  • ኢሜይል

    info@dashdc.org

Defend Yourself

  • እርስን መከላከል ሰዎችን ለማበረታታት ይሰራል  - በተለይ ለሴቶች እና ለጥቃት እና ጉዳት የተጋለጡ ሌሎችን  - ጥቃትን ለማቆም እና እራሳቸውን የሚሆኑበት አለም መፍጠር ይሰራል። ተማሪዎች ትንኮሳን፣ ጥቃትን ለማስወገድ እና ለመከላከል ክህሎቶች ይማራሉ፤ የሚያስፈራራን ሁኔታ በቃላት ለማስቆም፤ እና የተለመዱ ጥቃቶችን ለመከላከል አካላዊ ድርጊቶችን መጠቀም ይማራሉ። እርስን መከላከል የሚሰራው በሁሉም እድሜ ካሉ ሰዎች፣ ጾታዎች፣ እና በሁሉም የህይወት መንገድ ካሉ ጋር፣ ከትምህርት ቤቶች፣ የእምነት ቡድኖች፣ የስራ ቦታዎች፣ የማህበረሰብ ድርጅቶች፣ እና ሌሎች ጋር ነው።

  • ዋና

    301-608-3708

  • ድህረ ገጽ

    http://defendyourself.org

ማይ ሲስተርስ ፕሌስ

  • የቤት ውስጥ እና የቅርብ አጋር ጥቃት ተጎጅ ለሆኑ መጠለያ ይሰጣል።

  • የችግር መደመጫ መስመር፣

    202-749-8000

  • ዋና መስመር

    202-529-5991

  • ድህረ ገጽ

    http://dvhelpdc.org

  • ኢሜይል

    info@mysistersplace.org

ኤችኢአር የመቋቋሚያ ማዕከል

  • ኤችኢአር የመቋቋሚያ ማዕከል (ኤችኢአር) የተለያዩ የህይወት መሰናክሎችን እንዲቋቋሙ  እድሜያቸው ከ 18-25  ለሆኑ ለወጣት ሴቶች፣ ድጋፍ፣ ሃብቶች እና መምሪያዎችን ያቀርባል። የወጣት ሴት ህይወት ከኮረዳነት ወደ አዋቂነት በሚሸጋገርበት ጊዜ አስፈላጊ ድጋፎችን ማግኘት መቻል ወሳኝ እንደሆነ እናውቃለን። ኤችኢአር በዚህ ቁርጥ ወቅት ወጣት ሴቶችን የሚደግፈው የህይወትን መሰናክሎች ለማለፍ የተናጠል ድጋፍን በማቅረብ፤ እንደ ስራ፣ የጾታ ጤና፣ እና የግል መጎልበትን በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ለማህበረሰቡ የክህሎት ማዳበር ወርክሾፖችን በማሰናዳት፤ እናም ፈተናዎችን የማለፍ የህይወት ተሞክሮ ካላቸው ጋር እንዲሰለጥኑ በማገናኘት ነው።

  • ዋና

    202-643-7831

  • ድህረ ገጽ

    HERdc.org

  • ኢሜይል

    Info@HerResiliencyCenter.org

HIPS

  • ኤችአይፒኤስ በጾታ መቀየር እና ወይም በፍላጎት፣ በግፊት፣ ወይም በሁኔታዎች የተነሳ የአደንዛዥ እጽ ተጠቃሚነት የተነሳ ተጽእኖ ያረፈባቸውን ግለሰቦች እና ማህበረሰቦች ጤና፣ መብቶች፣ እና ክብሮች ያበረታታል። ኤችአይፒኤስ የሚያቀርበው ልባዊ የጉዳት ቅነሳ አገልግሎቶች፣ ጥብቅና፣ እና አክባሪ፣ የማያዳላ፣ እና ግላዊ ሃይል እና ውክልና የሚያጎናጽፍ የማህበረሰብ ተሳትፎን ነው።

  • 24/7 የስልክ መስመር

    ​1-800-676-4477

  • አድራሻ

    906 H Street NE Washington D.C. 20002

  • ድህረ ገጽ

    http://www.hips.org

ሀውስ አፍ ሩት

  • በቤት ውስጥ ሰለባ ለተጎዱ ሴቶች እና ለቤተሰቦቻቸው ቴራፒ እና ቤት ይሰጣሉ።

  • ዋና መስመር

    202-667-7001 x 320

  • አድራሻ

    5 Thomas Circle NW Washington, DC 20005

  • ድህረ ገጽ

    www.houseofruth.org

  • ኢሜይል

    houseofruth@houseofruth.org

የሴቶች ማዕከል

  • የሴቶች ማዕከል የሴቶች፣ የወንዶች እና የቤተሰቦችን የተለያዩ ፍላጎቶች በግል እና በቡድን የማማከር አገልግሎት እና የሥራ የምክር አገልግሎት ለመስጠት የቆመ ነው። የጾታዊ ትንኮሳ እና የቤት ውስጥ ጥቃት አገልግሎቶችን በሰለጠኑ፣ ፈቃድ ባላቸው እና ሩህሩህ ቴራፒስቶች አማካኝነት በመስጠት የተካኑ ናቸው። ማዕከሉ መጠነ ሰፊ አገልግሎቶች በነጻ እና በቅናሽና ገቢን መሰረት ባደረገ ክፍያ ይሰጣል።

  • ዋና መስመር

    202-293-4580

  • አድራሻ

    1025 Vermont Avenue NW #310 Washington, DC 20005

  • ድህረ ገጽ

    www.thewomenscenter.org

የተጠቂዎች ማገገሚያ ኔትወርክ

  • የተጠቂዎች ማገገሚያ ኔትወርክ የሚያቀርቡት የተሙዋላ የተጠቂ ጉዳይ አስተዳደር፣ ሲቪል እና ወንጀል ነክ ህጋዊ አገልግሎቶችን ነው። ኤንቪአርዲሲ ተጠቂዎችን ወደ ባህል ነክ ፕሮራሞች፣ መስማት የተሳናቸው አገልግሎቶች፣ እና ሌሎች ግልጋሎቶችን ማገናኘት ይችላል። 

  • ዋና መስመር

    202-742-1727

  • አድራሻ

    6856 Eastern Ave NW, Washington, DC 20012

  • ድህረ ገጽ

    http://www.nvrdc.org

የዲሲ የቤት ውስጥ ጥቃት ተከላካይ ሕብረት፣

  • በጾታዊ ጓደኝነት ጥቃት ላይ መረጃዎችን ይሰጣል

  • ዋና መስመር

    202-299-1181

  • አድራሻ

    5 Thomas Circle NW Washington, DC 20005

  • ድህረ ገጽ

    www.dccadv.org

  • ኢሜይል

    info@dccadv.org

የግልሰብ ማዕከል (The Person Center)

  • የፐርሰን ማዕከል የጦርነት ሰቆቃ አዙሪትን እና የቤት ውስጥ ጥቃትን በአፍሪካውያን ስደተኞች ላይ እንዲያበቃ ለማድረግ ተጠቂዎች ህይወታቸውን የሚያስተካክሉበት መንገዶችን ያቀርባል።

  • ዋና

    202-365-8213

  • ድህረ ገጽ

    http://thepersoncenter.org

  • ኢሜይል

    Info@thepersoncenter.org