• የህክምና ድጋፍ (ሜዲካል ኤይድ) ያግኙ

  • መታየት ያለባቸው አማራጮች፣

ምን ይጥብቃሉ

  • ሜድስታር (MedStar) ዋሽንግተን ሆስፒታል ማዕከል በወሲብ ጥቃት እና በፍቅር ግንኙነት ወይም በቅርብ የፍቅር ጓደኛ ለደረሰባቸው የወሲብ ተጠቂዎች የሕክም እና የአባዲና ምርመራ አገልግሎት በቀን 24 ሰዓት፣ 7 ቀናት በሳምንት አገልግሎት ይሰጣል። ምርመራው ተጠቂዎቹ በፈለጉት መልኩ የሚዘጋጅ ነው፣ ነገር ግን የማስረጃ መሰብሰብ፣ የተሟላ የሕክምና ምርመራ፣ የቅድመ መከላከያ መድሐኒቶች፣ እና ለረጅም ጊዜ ግብአቶች ሪፈራሎችን ሊያካትት ይችላል። እርስዎ እዛ እያሉ ለፖሊስ የደረሰቦትን ነገር ሪፖርት ማድረግ ማነጋገር ሊመርጡ ይችላሉ፣ ነገር ግን ዝግጁ እስከሚሆኑ ድረስ ፖሊስ ሆነ ማንኛውም ሰው አለማዋራት ይችላሉ። የእርስዎ መረጃ ሪፖርት ለማድረግ እስከምሚወስኑ ድረስ (እስከ 90 ቀናት ድረስ) ሊሰበሰብ እና በማይታወቅ መልኩ ሊያዝ ይችላል።

    ነፃ የኡበር ታክሲ አገልግሎት ወደ ሆስፒታሉ እንዲያገኙ እና በሆስፒታል ውስጥ በሚስጥር የእርስዎን ጉዳይ የሚከታተል ሰው እንዲመደብልዎ 1-844-443-5732 ላይ ይደውሉ።

የሚያምኑትን ሰው ይዘው ይምጡ

  • የተሻለ ከመሰለዎት የሚያምኑትን ሰው ይዘው ይምጡ። ጓደኛ፣ የቤተሰብ ዓባል፣ ወይም ልክ እንደ RA የዩንቨርስቲ ሠራተኛ ይዘው ይምጡ።

ገላዎን ለመታጠብ አይሞክሩ

  • ለወሲብ ጥቃት የፎረንሲክ ምርመራ ለማድረግ ገላዎን እና እጅዎን አይታጠቡ፣ በሰውነትዎ ላይ ውሀ አያፍስሱ፣ ጥርስዎን አይቦርሹ፣ ጸጉርዎን አያበጥሩ፣ መጸዳጃ ቤት አይጠቀሙ፣ አይብሉ/አይጠጡ፣ አያጭሱ፣ ማስቲካ አያኝኩ፣ ወይም ልብስዎን አይለውጡ። ይህ ከባድ ሊሆን ይችላል፣ ሆኖም ከላይ ከተጠቀሱት ማንኛውንም ካደረጉ ወንጀሉን ለፖሊስ ሪፖርት ለማድረግ ቢወስኑ አስፈላጊ የሆነ ማስረጃ ሊያጠፉ ይችላሉ።

ቅያሬ ልብሶችን ይዘው ይምጡ

  • ለወሲብ ጥቃት የፎረንሲክ ምርመራ ዝግጅት፣ ለራስዎ ምቾት እና ማስረጃውን ለማቆየት፣ ንጹህ መቀየሪያ ልብሶች እና በድርጊቱ ውስጥ አገልግሎት ላይ የዋሉ ነገሮችን የወረቀት ቦርሳ ውስጥ ጨምረው ይዘው ይምጡ።

ተጎጅዎችን እና ከጉዳት የተረፉትን መርዳት

  • ጓደኛዎ የወሲብ ጥቃት ከደረሰበት ለመርዳት የሚከተሉት መንገዶች አሉ፣

    • ይመኗቸው
    • አማራጮቻቸውን እንዲያዩ ይርዷቸው
    • ያዳምጧቸው
    • እርስዎም እንደተጎዱ ይወቁና እና ለራስዎም እርዳታን ይፈልጉ
    • የጥቃት ሰለባ በመሆናቸው ፈጽመው አይውቀሷቸው
    • ከመንካትዎ በፊት ይጠይቁ
    • እርስዎም እንደተጎዱ በማወቅ ለራስዎም እርዳታ ያግኙ

    ስለነዚህ መረጃዎች በዚህ የመረጃ ገጽ ከወንዶች አስገድዶ መድፈርን ማቆም የበለጠ ይማሩ። በ(http://www.mencanstoprape.org/images/stories/PDF/Handout_pdfs/supporting...)

    የወሲብ ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት እንዴት ያለጉዳት ጣልቃ መግባት እንደሚቻል ከወንዶች አስገድዶ መድፈርን ማቆም ይችላሉ ይወቁ።(http://www.mencanstoprape.org/images/stories/PDF/Handout_pdfs/interventi...)።