• በከተማው ውስጥ እርዳታ ያግኙ

  • ተሙዋጋዥ ያግኙ

የዲሲ የተጎጅ ማገገሚያ ኔትዎርክ (NVRDC)

  • ማንኛውም የሴንን (SANE) ምርመራ የሚፈልግ የወሲብ ጥቃት ሰለባ በNVRDC የተቀጠረ በሠለጠነ ባለሞያ ተቆርቋሪ በሆስፒታሉ ይገናኛል። ተቆርቋሪው በመጀመሪያ የችግር ምዕራፍ እና የማገገሚያ ሂደት ለወንጀል ሰለባው ካሳ፣ ቤት፣ የምክር አገልግሎት መጀመርን፣ ተከታታይ የህክምና እንክብካቤ እና ህጋዊ አገልግሎቶችን ያካተተ ድጋፍ ይሰጣል። NVRDC ከሜድስታር ዋሽንግተን ሆስፒታል ሴንተር፣ የዲሲ የተጎጅ አገልግሎቶች ቢሮ፣ እንዲሁም የዲሲ ሴን (SANE) ፕሮግራምን በጋራ የሚያስተዳድሩ የዲሲ የፎረንሲክ ነርስ መርማሪ ፕሮግራም ጋር አጋር በመሆኑ ኩራት ይሰማዋል። ተጎጅዎች በማገገሚያ ሂደት ላይ ባሉበት ጊዜ ተጠሪ እንዲኖራቸው ተከታታይ የኬዝ ማኔጅመንት ይኖራል። የኬዝ ማኔጅመንት ክፍሉ ዓላማ የተጎጅውን ተከታታይ ፍላጎቶች ማሟላት፣ ተጎጅዎችን የሚያበረታት ድጋፍ እና ጥብቅና መስጠት እንዲሁም የተጎጅው ፍላጎቶች በNVRDC አገልግሎቶች ወይም ታማኝ በሆኑ ተቀባይ አጋሮች አማካኝነት መሟላታቸውን ማረጋገጥ ነው። የሚሰጡት አገልግሎቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፣ ሆኖም በእነዚህ ብቻ አይወሰኑም፣

    • የደህንነት እቅድ
    • የተጎጅ ማሳታወቂያ
    • የወንጀል ሰለባዎች የካሳ እርዳታ
    • የወንጀል ፍትህ ድጋፍ እና ወደ ፍርድ ቤት ይዞ መሄድ
    • የማስተርጎም አገልግሎቶች
    • የማህበራዊ የህግ አገልግሎቶች
    • ለተጎጅው መብቶች ውክልና
    • መረጃ እና ወደ ሌላ መምራት

  • ዋና መስመር

    202-742-1720

  • አድራሻ

    6856 Eastern Avenue NW Washington, DC 20012

  • ድህረ ገጽ

    www.nvrdc.org

ከጉዳት የተረፉ እና የአቅም ግንባታ ጠበቆች (SAFE)

  • ከጉዳት የተረፉ እና የአቅም ግንባታ ጠበቆች (SAFE) በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚኖሩ ከቤት ውስጥ ጥቃት ለተረፉ የድንገተኛ አገልግሎቶች፣ በፍርድ ቤት ጥብቅና እና የሥራአት ማሻሻል በማድረግ ደህንነት እና ራስን ማስተዳደር መቻላቸው ያረጋግጣሉ። በቅርብ አጋርዎ፣ በጾታዊ ግንኙነት ወይም ቤት ውስጥ በተፈጠረ ጥቃት ሰለባ ከሆኑ SAFE ያሉዎትን አማራጮች እንዲያዩ በማነጋገር ሊረዳዎት ይችላል።

  • ዋና መስመር

    202-879-7851

  • ድህረ ገጽ

    http://dcsafe.org/