• በከተማው ውስጥ እርዳታ ያግኙ

  • ተጨማሪ ግልጋሎቶች

  • የመኖሪያ ቤት አገልግሎቶች

ዳሽ (DASH)

  • ዳሽ በችግር ውስጥ ለወደቁ ሴቶች እና ሕፃናት የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ እና ጊዜያዊ ደህንነቱ የተጠበቀ መኖሪያ ያቀርባል እና በጣም አደገኛ የሆነ የመኖሪያ ሁኔታን ለመልቀቅ ወይም ለመቀየር ግብአቶችን ያቀርባል።  እነዚህ አገልግሎቶች የሚያካትቱት ሊዝ ከመቀየር እና ከማቋረጥ ጋር ግብአቶች፣ የቤት አድሎ ማድረግን መቋቋሚያ ግብአት፣ አዲስ ቤት የማግኛ ግብአት፣ እና የገንዘብ እና የመኖሪያ ቤት ነፃነት በድጋሚ ማቋቋም ናቸው።

  • ዋና

    202-742-1728

  • ድህረ ገጽ

    http://dashdc.org

  • ኢሜይል

    info@dashdc.org

ዲሲ ሴፍ (DC SAFE)

  • ሴፍ ለአስቸኳይ የመጠለያ ችግር፣ ለደህንነት ዕቅድ፣ የሕግ መረጃ፣ የተጠቂውን ቤት የሚጠብቅ እገዛ፣ ለምግብ፣ አውቶብስ ትኬት፣ እና ለሕፃናት እና ለልጆች አቅራቦቶች፣   ድንገተኛ ጊዜ ጊዜያዊ የጥበቃ ትዕዛዝ (ETPO) ሂደት መዳረስ፣ እና ሴፍ (SAFE) ቦታ የሚባል ድንገተኛ መኖሪያ ፕሮግራም ለማቅረብ ይሟገታል።

    ሴፍ ቦታ ለቤት ውስጥ ጥቃት ተጠቂ ለሆኑ እና ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ላሉ ቤተሰቦች የአስቸኳይ ጊዜ መጠለያ ለ 20 ቀናት ያቀርባል። ሴፍ ቦታ ቤተሰቦች ሊያገግሙበት የሚችሉበት፣ እራሳቸውን ወዲያውኑ እንዲጠብቁ አስፈላጊውን የማህበራዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እና ስለወደፊቱ ሕይወታቸው የረጅም ጊዜ ውሳኔዎችን እንዲወስኑ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ጸጥ ያለ፣ ሙሉ ለሙሉ የተሟላ አፓርትመንት ያቀርባል። ዲሲ ሴፍ ሠራተኞች እና አማካሪ እነዚህ አስፈላጊ ቀጣይ ቅደም ተከተሎች ላይ እገዛ ለማድረግ በቦታው ላይ ይገኛሉ።


  • ዋና

    202-879-7851

  • ድህረ ገጽ

    http://dcsafe.org

ሃውስ ኦፍ ሩት (House of Ruth)

  • ሃውስ ኦፍ ሩትስ በቤት ውስጥ ጥቃት ለሚጠቁ ሴቶች እና ቤተሰቦች መኖሪያ ቤት እና ቴራፒ አገልግሎት ይሰጣል።

  • ዋና

    202-667-7001 x 320

  • አድራሻ

    5 Thomas Circle, NW Washington, DC 20005

  • ድህረ ገጽ

    www.houseofruth.org

  • ኢሜይል

    houseofruth@houseofruth.org

ማይ ሲስተርስ ፕሌስ (My Sister’s Place)

  • ማይ ሲስተርስ ፕሌስ ለቤት ውስጥ እና/ወይም የቅርብ የፍቅር ጓደኛ ጥቃት ተጠቂዎች መጠለያ ነው።  በተጨማሪም፣ ነፃ፣ የሚስጥር የስልክ መሰመሩ 24/7/365 ይገኛል። ድርጅቱ ጊዜያዊ ወደ ቋሚ መኖሪያ ቤት በነፃ የስልክ መስመሩ በኩል ለአስቸኳይ ችግር የተሟላ ቀጣይ አገልግሎት ይሰጣል።

  • የስልክ መስመሮች

    202-529-5991

  • ዋና

    202-529-5261

  • ድህረ ገጽ

    https://mysistersplacedc.org

  • ኢሜይል

    info@mysistersplace.org

የቨርጂኒያ ዊሊያምስ የቤተሰብ አገልግሎት ማዕከል

  • የቨርጂኒያ ዊሊያምስ የቤተሰብ አገልግሎት ማዕከል (ቪደብሊውኤፍአርሲ) በዲስትሪክቱ ውስጥ የመኖሪያ አለመረጋጋት ላጋጠማቸው ህጻናት እና ቤት አልባ  ልጅ ያላቸው ቤተሰቦች ማዕከላዊ አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል ነው። የቪደብሊውኤፍአርሲ ሰራተኛ ከቤተሰቦች ጋር አብሮ በመስራት ቤት አልባነትን የሚከላከለው በቤት ውስጥ የሚቆዩበትን መንገዶች ላይ በማተኮር፣ መጠለያ ሳይገቡ የመኖሪያ ቤት አማራጮችን እንዲያገኙ በመርዳት፣ እና እንደ የህዝብ ጥቅማ ጥቅሞችን፣ የህጻን እንክብካቤን፣ እና የስራ እርዳታን የመሰሉ እርዳታዎችን ያቀርባል።

  • ዋና መስመር

    202-526-0017

  • አድራሻ

    920-A Rhode Island Avenue, NE Washington, DC 20018

  • ድህረ ገጽ

    http://www.dccfh.org/programs/housing/virginia-williams-family-resource-center