• በከተማው ውስጥ እርዳታ ያግኙ

  • የብዙ ቋንቋ አገልግሎቶች

የኤሽያ/ፓስፊክ ደሴት ነዋሪ የቤት ውስጥ ጥቃት ግብአት ፕሮጀክት

  • DVRP ከቤት ውስጥ ጥቃትና ጾታዊ ጥቃት ለተረፉ ከ20 በላይ በሆኑ የእስያ ቋንቋዎች ነጻ እና ሚስጥራዊ አገልግሎቶች ይሰጣል። DVRP የገቢ ምንጫቸው፣ የኢሚግሬሽን ሁኔታቸው ወይም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታቸው ከግምት ሳይገባ ከቤት ውስጥ ሁከት ለተረፉ ደህንነታቸውን ለማሻሻል ይጥራል።

  • የችግር መደመጫ መስመር

    202-464-4477

  • ዋና መስመር

    202-464-4477

  • ድህረ ገጽ

    http://dvrp.org/

የሜትሮፖሊታን ፖሊስ መምሪያ - የብዙ ቋንቋ አገልግሎቶች

  • ከ150 በላይ በሆኑ የብዙ ቋንቋ አገልግሎቶች ይሰጣል።

  • ዋና መስመር

    202-727-9099

MPD የአስያዊያን አገናኝ ክፍል

MPD የላቲኖ አገናኝ ክፍል

አዩዳ፣

  • የጾታ ጥቃት ለደረሰባቸው ስደተኞች እነኝህን አገልግሎቶች እንሰጣለን፤

    የህግ አገልግሎቶች፣ የአዩዳ ሠራተኞች የቤት ውስጥ ሁከት እና የጾታ ጥቃት ለደረሰባቸው ስደተኞች የቤተሰብ ህግ እና የኢሚግሬሽን ጉዳይን ጨምሮ ሰፋ ያለ የህግ አገልግሎት ይሰጣሉ። የአዩዳ ተቆርቋሪዎች ደንበኞችን በተለያዩ የኢሚግሬሽን ጉዳዮች ጊዜያዊ እና የህዝብ ጥበቃ ትዕዛዞችን ጨምሮ፣ ህጋዊ መለያየት፣ ፍች፣ የልጅ ጥበቃ፣ መጎብኘት እና የልጅ ድጋፍን በተመለከተ ይረዳሉ።

    በተጨማሪም፣ አዩዳ ከላይ የተጠቀሱትን ትዕዛዞችን የመለወጥ፣ የማስረዘም፣ እና የማስፈጸም እና ከላይ ለተጠቀሱት ትዕዛዞች የህዝብ ፍርድ መጣስን በተመለከተ ይሠራል። በተጨማሪ አዩዳ የህዝብ ጥበቃ ትዕዛዝ የወንጀል፡ጥሰቶችን በተመለከተ ይሠራል።

    ማህበራዊ አገልግሎቶች፣ አዩዳ የቤት ውስጥ ሁከት ሰለባ ለሆኑ እና የጾታ ጥቃት ለደረሰባቸው በችግራቸው ጣልቃ መግባት እና በአጠቃላይ ጉዳይ የመከታተል አገልግሎቶች ይሰጣል። የአዩዳ የማህበራዊ አገልግሎት ሠራተኞች ደንበኞች ተገቢውን የማህበረሰብ ሪሶርሶች በማግኘት አስቸኳይ እና ጊዜያዊ መጠለያ፣ ምግብ፣ ልብስ፣ ህክምና እና የአእምሮ ጤና እንክብካቤ ለእራሳቸው እና ለልጆቻቸው እንዲያገኙ ይረዳሉ።

    አብዛኞቹ የአዩዳ የቤት ውስጥ ሁከት እና የጾታ ጥቃት ደንበኞች የህግ እርዳታ ከአዩዳ ቢያገኙም፣ ማህበራዊ አገልግሎቶች ለማግኘት ይህንን ማድረግ የለብዎትም።

  • ዋና መስመር

    202-387-4848

  • አድራሻ

    6925 B Willow Street NW Washington, DC 20012

  • ድህረ ገጽ

    http://ayuda.com/

የመካከለኛው አሜሪካ የግብአት ማዕከል (CARECEN)

  • CARECEN በዲሲ ለተፈጸመ ወንጀል በሁለት ቋንቋ (እንግሊዝኛ/ስፓንሽና) እርዳታ ይሰጣል። CARECEN ጥቃት ለደረሰባቸው ኢሚግራንቶች ለU ቪዛ ብቁነታቸውን ይመረምራል፣ ለወንጀል ጥቃት ካሳ ማመልከቻ ማስገባት፣ እንዲሁም አስፈላጊ ከሆነ የምክር እና/ወይም የህክምና እርዳታ ሪሶርሶች እንዲያገኙ

    CARECEN አለቀጠሮ ሀሙስ ከሰዓት በኋላ ከ2 እስከ 4:30pm አገልግሎት መስጠት እና አስቀድሞ ስልክ በመደወል ሌሎች ቀጠሮዎች ማስያዝ ይቻላል።

  • ዋና መስመር

    202-328-9799

  • አድራሻ

    1460 Columbia Road, NW Suite C-1 Washington, DC 20009

  • ድህረ ገጽ

    www.carecendc.org

የላቲን አሜሪካን ወጣቶች ማዕከል (LAYC)

  • 202-319-2258 (የጤና ግንኙነቶች ፕሮግራም አስተባባሪ ቢሮ)
    202-810-5906 (የሞባይል ፕሮግራም አስተባባሪ)

    የላቲን አሜሪካን ወጣቶች ማዕከል (LAYC) ጤና ግንኙነት ፕሮግራም በርካታ የባህል እና ቋንቋ ነክ የሆኑ (እንግሊዝ-ስፓኒሽ) በተለይ በወጣት የላቲኖ ጋንጎች ላይ ያተኮረ የተራፊ ጥብቅና አገልግሎቶች ይሰጣል። ጠበቆቻችን የችግር ጣልቃ ገብነት፣ የግል ምክር፣ የትምህርት ወይም የድጋፍ ቡድኖች ማግኘት እና ወደ አካባቢ አገልግሎት ሰጭዎች እና በLAYC የሚሰጡ ሌሎች አገልግሎቶች የመምራት ድጋፍ ይሰጣል። ዕድሜያቸው ከ13 እስከ 24 ዓመት ለሆነ ከጾታዊ ጥቃት፣ ከጾታዊ ጓደኛ/የቤት ውስጥ ሁከት ወይም ጤናማ ካልሆነ ግንኙነት ለተረፉ ወጣቶች የድጋፍ አገልግሎቶች ይሰጣል።

    LAYC የተለያዩ ባህል ያላቸውን ወጣቶች ብዙ-ባህል ያካተተ፣ ሁሉን ያጠቃለለ የተሳካ የወጣቶችን ማኅበራዊ፣ አካዳሚ እና የሥራ ፍላጎታቸውን የሚያሟላና ወደ አዋቂነት እንዲሸጋገሩ የሚረዳ በርካታ የወጣቶች አገልግሎቶችን የሚሰጥ ድርጅት ነው።

  • ዋና መስመር

    202-319-2225

  • አድራሻ

    1419 Columbia Road NW Washington, DC 20009

  • ድህረ ገጽ

    www.layc-dc.org

የሜሪ ሲንተር

  • 3912 Georgia Avenue NW
    Washington, DC 20011 

    ከቤት ውስጥ ሁከት ለተረፉ ድጋፍ እና የኬዝ ማኔጅመንት ይሰጣል። ሠራተኞቹ 30 ቋንቋዎች ይናገራሉ።

  • ዋና መስመር

    202-420-7082

  • ለቤት ውስጥ ጥቃት ስምና ስልክ: ጇዋና ማርኩየዝ፣

    202-420-7196

  • አድራሻ

    2333 Ontario Road NW Washington, DC 20009

  • ድህረ ገጽ

    www.maryscenter.org

ሚል ሙጀርስ፣

  • ሚል ሙጀርስ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ከቤት ውስጥ ሁከት እና ጾታዊ ጥቃት ለተረፉ የስፓኒሽ ቋንቋ ተናጋሪዎች በኢሚግሬሽን ህግ አካባቢ ቀጥተኛ የህግ አገልግሎቶች ይሰጣል።

  • ዋና መስመር

    202-560-5237

  • አድራሻ

    1419 V Street NW, Suite 301 Washington, DC 20009

  • ድህረ ገጽ

    www.milmujeres.org

  • ኢሜይል

    washingtondc@milmujeres.org

አሜሪካን መጎብኘት

  • ለበለጠ መረጃ የሀገርዎን ኤምባስ ወይም ኮንሱሌት ያነጋግሩ። የሀገርዎን ኤምባሲዎች ወይም ኮንሱሌቶች ዌብሳይት እዚህ በአሜሪካ ማግኘት ይችላሉ። http://www.state.gov/s/cpr/rls/dpl/32122.htm

የብዙ ቋንቋ አገልግሎቶች - የውጭ ሀገር መጎብኘት

ስደተኛ ህጋዊ ግልጋሎት ማዕከል

  • ሁሉም በዩናይትድ ስቴተስ ያሉ ህዝቦች፣ በማንኛውም የስደተኝነት ሁኔታ ላይ ያሉ፣ በዩ ኤስ ህገ መንግስት ስር ያሉ የተወሰኑ መብቶች እና ጥበቃዎች አሉዋቸው። ቀያይ ካርዶች የተፈጠሩት ህዝቦች መብቶቻቸውን እንዲያረጋግጡ እና ከህገ መንግስታዊ ጥሰቶች እራሳቸውን እንዲከላከሉ ለመርዳት ነው። መብቶችዎን ማወቅ እና ማረጋገጥ በብዙ ሁኔታዎች ላይ ትልቅ ልዩነት ሊፈጥር ይችላል፤ ለምሳሌ የአይሲኢ ወኪሎች ወደ ቤት ከመጡ። ቀያይ ካርዶች መብቶችዎን እንዴት እንደሚያረጋግጡ ወሳኝ መረጃ ይሰጣሉ፤ ይህም ለአይሲኢ ወኪሎቹ ግለሰቡ መብቶቻቸውን እያረጋገጡ እንደሆነ ማብራሪያን ማካተት ይጨምራል።

    ነጻ ቀያይ ካርዶችዎች ለማዘዝ፣ እባከዎትን ጥያቄዎን ወደ ሚከተለው ኢሜይል ይላኩ። ስምዎን፣ ድርጅትዎን፣ አድራሻዎን፣ እና የሚፈልጉትን የካርድ ብዛት ይጨምሩ። redcards@ilrc.org

    ቀያይ ካርዶችን እንዴት መጠቀም ፡ ማሳያዎች

    የማህበረሰብ ግልጋሎቶች

  • ድህረ ገጽ

    https://www.ilrc.org/red-cards

የግልሰብ ማዕከል (The Person Center)

  • የፐርሰን ማዕከል የጦርነት ሰቆቃ አዙሪትን እና የቤት ውስጥ ጥቃትን በአፍሪካውያን ስደተኞች ላይ እንዲያበቃ ለማድረግ ተጠቂዎች ህይወታቸውን የሚያስተካክሉበት መንገዶችን ያቀርባል።

  • ዋና

    202-365-8213

  • ድህረ ገጽ

    http://thepersoncenter.org

  • ኢሜይል

    Info@thepersoncenter.org

የደህንነት ዕቅድ

ከሕግ አስከባሪዎች ጋር በሚነጋገሩበት ሰዓት ስለመብቶችዎ መመሪያ

  • ከሕግ አስከባሪዎች ጋር በሚነጋገሩበት ሰዓት ስለመብቶችዎ መመሪያ። ይሄ መመሪያ የሚያካትተው፡

    • የኢምግሬሽን ኤጀንቶች፣ ፖሊስ ወይም ኤፍቢአይ ሰዎችን የተለያዩ ቦታዎች ላይ ሲያገኙ ጊዜ ምን ማወቅ እንዳለብዎ እና ምን ማድረግ እንዳለብዎ
    • የእስር ማዘዢያን እንዴት እንደሚያነቡ መረጃ
    • በማንኛውም ሁኔታ ላይ እርስዎ እና ቤተሰብዎ ማስታወስ ያለባችሁ አስራ ሁለት ነገሮች
    • የድንገተኛ ጊዜ ዕቅድ ማረጋገጫ ዝርዝርዎ
    • የድንገተኛ ጊዜ የስልክ ማውጫ ወረቀትዎ
    • ከኢሚግሬሽን እስር ቤት ወይም ፖሊስ ጣቢያ የሚወዱት ሰው ሲደውል ማድረግ የሚገባዎ ዕቅድ
    • የሥራ ቦታ ዕቅድ ማረጋገጫ ዝርዝርዎ

    መመሪያ

መብትዎን እንዴት እንደሚያስከብሩ

  • በዲሲ ውስጥ ኢሚግራንት ለሆኑ ወላጆች መመሪያ፣ “በ ICE ከታሰርኩኝ ምን ላድርግ”። 

ኖርዝዌስት ኢሚግራንት መብቶች ፕሮጀክት (Northwest Immigrant Rights Project)

  • በማህበረሰብ ውስጥ በሲሳም ስትሪት የተፈጠረው የኬር፣ ኮፕ፣ ኮኔክት ግብአት ወላጆች ጭንቀት እንዲቋቋሙ እና የልጆችን ደህንነት ይጠብቃል።

ኬር - ኮፕ - ኮኔክት (Care – Cope - Connect)

  • በማህበረሰብ ውስጥ በሲሳም ስትሪት የተፈጠረው የኬር፣ ኮፕ፣ ኮኔክት ግብአት ወላጆች ጭንቀት እንዲቋቋሙ እና የልጆችን ደህንነት ይጠብቃል።

  • ድህረ ገጽ

    http://first5association.org/care-cope-connect/