• በከተማው ውስጥ እርዳታ ያግኙ

  • የህግ አገልግሎቶች

ብሬክ ዘ ሳይክል፣

  • ብሬክ ዘ ሳይክል በዋሽንግተን ዲሲ የጾታዊ ግንኙነት ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ወጣቶች ደህንነትንና ፍትህን እንዲያገኙ ህጋዊ አገልግሎቶችን ይሰጣል። ብሬክ ዘ ሳይክል በሚከተሉት ህጋዊ ጉዳዮች ዙሪያ እርዳታ ይሰጣል፣

       • ጥበቃ ወይም የእገዳ ትዕዛዞች ማግኘት
       • የእገዳ ትዕዛዝ ጥሰቶች አሠራር
       • የልጅ ማሳደግ
       • የልጅ ድጋፍ
       • ጉብኝት
       • ፍቺ 

  • ዋና መስመር

    202-849-6289

  • ድህረ ገጽ

    www.breakthecycle.org

  • ኢሜይል

    legalservices@breakthecycle.org

የሜትሮፖሊታን የፖሊስ መምሪያ - የተጎጅ አገልግሎቶች ቅርንጫፍ

  • የሜትሮፖሊታን ፖሊስ መምሪያ (MPD) ዓላማ ሁሉንም ተጎጅዎች በክብር፣ በንቃት እና በርህራሄ ማስተናገድ ነው። ስለሆነም የመምሪያው የተጎጅ ስፔሻሊስቶች ክፍል በቤት ውስጥ ጥቃት እና በጾታ ጥቃት ለደረሰባቸው እና ከጉዳት ለተረፉ ድጋፍ፣ መረጃ እና ወደ ሌላ ቦታ የመምራት አገልግሎት ይሰጣል። የተጎጅ ስፔሻሊስቶቹ ለተጎጅዎች/ከጉዳት ለተረፉ ለማበረታታት ድጋፍ ሰጪ እና አስተላላፊ መስመር ሆነው ያገለግላሉ:: በተጨማሪም የተጎጅ ስፔሻሊስቶች ክፍል ከማህበረሰቡ ጋር ግንኙነቶችን በመመስረት እና ለተጎጅዎች እና ቤተሰቦቻቸው የመረጃ ምንጭ በመሆን የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል ነው።

  • ዋና መስመር

    202-724-4339

  • አድራሻ

    300 Indiana Ave, NW, Room 3121 Washington, DC 20001

  • ድህረ ገጽ

    http://mpdc.dc.gov/page/victim-specialists-unit-vsu

የሜትሮፖሊታን የፖሊስ መምሪያ - የጾታዊ ጥቃት ክፍል

  • የጾታዊ ጥቃት ክፍል ወደ ዋሽንግተን ሆስፒታል ሴንተር ማጓጓዣን ሊያመቻች ይችላል፣ ለወንጀል ሰለባ ካሳ ፕሮግራም ለማመልከት እርዳታ ሊሰጥ ይችላል፣ እንዲሁም ክሶችን (የወንጀል ሰለባ/ከጉዳት ለተረፉ ክሶችን ለማቅረብ 90 ቀናት አለው) ሳይመሰርት ማስረጃን ሊወስድ ይችላል::

  • ዋና መስመር

    202-727-3700

  • አድራሻ

    300 Indiana Avenue, NW, Room 3042 Washington, DC 20001

  • ድህረ ገጽ

    http://mpdc.dc.gov/page/sex-assault-unit

MPD የቤት ውስጥ ጥቃት ክፍል

  • ትራንስፖርት በማዘጋጀት እና ማስረጃዎችን በመሰብሰብና የፖሊስ ሪፖርት በማስመዝገብ ይረዳል።

  • ዋና መስመር

    202-727-7137

  • አድራሻ

    300 Indiana Avenue NW, Room 3156 Washington, DC 20001

  • ድህረ ገጽ

    http://mpdc.dc.gov/node/139072

MPD የጌይ እና ሌዝቢያን አስተባባሪ ክፍል

የሜትሮፖሊታን የፖሊስ መምሪያ - የወጣት ምርመራዎች ቅረንጫፍ

MPD የወጣቶች ምርመራዎች ቅርንጫፍ

የዲሲ የበጎ ፈቃድ ጠበቆች ፕሮጀክት

  • አነስተኛ ገቢ ላላቸው ለዲሲ ነዋሪዎች በተለይ በህግ ጥበቃ ትዕዛዝ ውስጥ ያሉ፣ ከቤት ውስጥ የጥቃት ሰለባ የተረፉ፣ የልጅ አበል፣ ጉብኝት፣ ፍች፣ የልጅ ድጋፍ እና የኢምግሬሽን ጉዳዮች በተመለከተ ከፍተኛ ጥራት ያለው ነጻ የህግ አገልግሎቶችን ይሰጣል።

  • ዋና መስመር

    202-885-5542

  • አድራሻ

    5335 Wisconsin Ave NW Suite 440 Washington, DC 20015

  • ድህረ ገጽ

    www.dcvlp.org

  • ኢሜይል

    cgwilliam@dcvlp.org

የዲሲ ተጎጅ ማገገሚያ ኔትዎርክ (NVRDC)

  • ማስታወሻ፣ የዲሲ ተጎጅዎች ማገገሚያ ኔትዎርክ እነኝህን አገልግሎቶች ከጾታዊ ጥቃት በተጨማሪ ለጠቅላላ ጉዳት ሰለባዎች ሊሰጥ ይችላል።

    ለፈውስ እና ጥብቅና አገልግሎቶች፣
    የዲሲ ተጎጅዎች ማገገሚያ ኔትዎርክ በችግር ጊዜ ጣልቃ በመግባት እርዳታ ይሰጣል፣ እንዲሁም የአጭር ጊዜ የአካላዊ ጤና፣ የዓዕምሮ ጤና እና የግል ፍላጎቶች ግምገማ በማድረግ እነዚህን ፍላጎቶች ቀጥተኛ በሆነ መንገድ አገልግሎት በመስጠት ወይም ወደሚመለከታቸው በመምራት ፍላጎቶቹን ለማሟላት ይሞክራል። የዲሲ ተጎጅ ማገገሚያ ኔትዎርክ የሚከክተሉትን የኬዝ ማኔጅመንት አገልግሎቶች፣ የደህንነት እቅድ፤ ተጎጅን ማሳወቅ፤ የወንጀል ሰለባ ካሳ እርዳታ፤ የወንጀል ፍትህ ድጋፍ እና ፍርድ ቤት ይዞ መሄድ፤ የትርጉም አገልግሎቶች፤ የማህበራዊ ህጋዊ አገልግሎቶች፣ ለተጎጅው መብቶች ውክልና እና የሪሶርስ መረጃና ወደ ሌላ መምራትን እና ሊሎችንም ጨምሮ ይሰጣል።

  • ዋና መስመር

    202-742-1720

  • አድራሻ

    6856 Eastern Ave, Washington, DC 20012

  • ድህረ ገጽ

    www.nvrdc.org

ብሔራዊ የወንጀል ሰለባዎች ማዕከል

ብሔራዊ የወንጀል ሰለባዎች ማዕከል - ብሔራዊ የጾታዊ ግንኙነት ጥቃት የእርዳታ መስመር

  • “ፍቅር ነው”ን ወደ 22522 ቴክስት ያድርጉ

    የጾታዊ ግንኙነት ጥቃት ለሚያጋጥማቸው በተለይ ለታዳጊዎች እና ለወጣት ታዳጊዎች እንዲሁም ለጓደኞቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው የተዘጋጀ የ24 ሰዓት በቀን ሳምንቱን በሙሉ የስልክ ሆትላይን እና ኦንላይን ውይይት:: አገልግሎቶቹ ነፃ ናቸው እንዲሁም በሚሥጥር ይያዛሉ።

  • ሆትላይን

    1-877-331-9474

  • TTY

    1-866-331-8453

  • ድህረ ገጽ

    www.loveisrespect.org

የዩናይትድ ስቴትስ አቃቤ ቢሮ

  • የተጎጅ ምስክር እርዳታ፣ 202-252-713

    የዲሲ የዩናይትድ ስቴትስ አቃቤ ቢሮ ከሥራው መጠን እና ብዛት ከሌሎች አቃቤ ቢሮዎች የተለየ ነው። ለሀገሪቱ ዋና ከተማ የፌደራል እና የአካባቢ ህግ አስከባሪ በመሆን ያገለግላል። በአካባቢው በኩል፣ ከአነስተኛ የዕጽ መጠቀም ሁኔታዎች እስከ የጾታዊ ጥቃት እና የመግደል ወንጀል ህግ ማስከበርን ያጠቃልላል። በፌደራሉ በኩል፣ከልጆች ወሲበ ነክ ጽሁፎች እስከ ጋንግ፣ የገንዘብ ማጭበርበር እና ሽብረኞችን የሚመለከት ህግ ማስከበርን ያጠቃልላል። በሁለቱም ኃላፊነቱ፣ ቢሮው ለኮሎምብያ ዲስትሪክት ኗሪዎች አፋጣኝ መልስ ሰጪ እና ተጠያቂ ለመሆን የቆመ ነው። ጉዳዩ ወደ የዩናይትድ ስቴትስ አቃቤ ቢሮ ከተመራ እና ተቀባይነት ካለው የአቃቤ ቢሮው ለተጎጂ እርዳታ መስጠት ይችላል።

    • የጾታ ጥፋት እና የቤት ውስጥ ሁከት ክፍል፣ የጾታ ጥፋት እና የቤት ውስጥ ብጥብጥ ክፍል ሁሉንም ውንጀሎች እና የጾታዊ ጥቃቶች ወንጀል (የአዋቂዎች እና የልጆች ሰለባዎችን የሚያካትቱ)፣ የልጅ አካላዊ ጥቃት እና የቤት ውስጥ ሁከት - ቤት ሰርሳሪነት፣ መጥለፍ፣ መስረቅ፣ መከታተል እና የመሳሪያ ጥቃትን ጨምሮ ህግ የማስከበር ኃላፊነት አለው። የጾታ ጥፋት እና የቤት ውስጥ ሁከት ክፍል እያንዳንዱን ጉዳይ ከላይ ወደታች በህግ ያስከብራል፣ ማለትም አንድ ህግ አስከባሪ ከወንጀለኛው መጀመሪያው ቃለ መጠይቅ፣ ምርመራ እና የክስ ሂደት እስከ ፍርድ ወይም ሌሎች ሁኔታዎች ድረስ ማለት ነው። ክፍሉ በተጨማሪ በኢንተርኔት የሚደረግ የልጅ ጾታዊ ጥቃት እና በሰው መነገድን መርምሮ ለፍርድ ያቀርባል። የክፍሉ ህግ አስከባሪዎች ከጉዳተኛ/ምስክር ረዳት ክፍል ተቆርቋሪዎች ጋር በመመደብ በምርመራው እና በፍርዱ ሂድት በሙሉ በቅርብ ይሠራሉ።

    • የጉዳተኛ ምስክር ረዳት ክፍል፣ የጉዳተኛ ምስክር ረዳት ክፍል የከባድ ወንጀል ሰለባ ለሆኑ እና ምስክሮች በወንጀል ፍርድ ሥራዓት ውስጥ በሚገኙበት ጊዜ እርዳታ ይሰጣል። ክፍሉ ሰለባ ለሆኑት የወንጀል ፍርድ ሥርዓት እንዴት እንደሚሠራ እንዲረዱ እና በካሳና በአገልግሎት ይረዳል።   

  • ዋና መስመር

    202-252-7566

  • TTD Line

    202-514-7558

  • ድህረ ገጽ

    http://www.justice.gov/usao/dc/

  • ኢሜይል

    dc.outreach@usdoj.gov