• ለሆነ ሰው ያናግሩ

  • በኦንላይን ይወያዩ

የመከላከያ ሠራዊት መምሪያ (DoD) የእርዳታ መስመር

  • የመከላከያ ሠራዊት መምሪያ (DoD) አስጊ ያልሆነ የእርዳታ መስመር የጾታ ጥቃት ለደረሰባቸው የመከላከያ ሠራዊት ዓባላት ዋና የችግር ድጋፍ ሰጭ ነው። አስጊ ያልሆነ የእርዳታ መስመር አንድ ለአንድ በአካል ድጋፍ እና መረጃ ለዓለም አቀፍ የመከላከያ ሠራዊት ህብረተሰብ ይሰጣል። አገልግሎቱ ሚስጥራዊ፣ ማንነትን የማይገልጽ፣ የተጠበቀ እና ለተጎጅዎች በማንኛውም ጊዜ፣ ሰዓት እና ቦታ አስፈላጊውን እርዳታ በሙሉ ዓለም 24 ሰዓት በቀን ሳምንቱን በሙሉ ይሰጣል።

  • 24/7 ቀጥታ መስመር

    877-995-5247

  • ድህረ ገጽ

    www.safehelpline.org

የብሔራዊ ጾታዊ ጥቃት የኦንላይን ሆትላይን

  • አስገድዶ መድፈር፣ ትንኮሳ እና ኢንሰስት ብሔራዊ ኔትዎርክ (RAINN) ከጾታዊ ጥቃት ለተረፉ ነጻ፣ ሚስጥራዊ፣ ማንነትን ይፋ የማያደርግ የውይይት አገልግሎትን የሚሰጠውን የብሔራዊ ጾታዊ ጥቃት ኦንላይን ቀጥተኛ መስመርን ያንቀሳቅሳል። አስገድዶ መድፈር፣ ትንኮሳ እና ኢንሰስት ብሔራዊ ኔትዎርክ (RAINN) በጾታዊ ጥቃት ለተጎዱ የመከላከያ መምሪያ ዓባላት የመከላከያ መምሪያን የሚያስተማምን ኦንላይን የእርዳታ መስመር እና የስልክ ቀጠታ መስመሮች ሥራ ላይ ያውላል።

     

  • ድህረ ገጽ

    https://ohl.rainn.org/online/

ዲሲ ተጠቂዎች ነፃ የስልክ መስመር

  • የዲሲ ተጠቂዎች ነፃ የስልክ መስመር የመስመር ላይ ውይይት የሚገኘው ከሰኞ-አርብ ከ12 ከምሳ በኋላ-5 ጠዋት ድረስ ነው። የተጠቂ ድጋፍ ሰጪ ስፔሻሊስት መረጃ፣ ድጋፍ እና ሪፈራሎች ለአከባቢው ድርጅቶች እና በማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ግብአት አቅራቢዎች እነዚህን ያቀርባሉ: 

    • የወንጀል ተጠቂ ካሳ ፈንድ ማግኘት ላይ 
    • የሕክምና እና የአባዲና ምርመራዎች
    • መኖሪያ ቤት 
    • የሕግ ድጋፍ
    • የአዕምሮ ጤና ማማከር እና ድጋፍ ሰጪ ቡድኖች
    • እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎች የግል ድጋፍ ሰጪዎች

  • ድህረ ገጽ

    http://dcvictim.org

ላቭ ኢዝ ሪስፔክት (Love is Respect)

  • ላቭ ኢዝ ሪስፔክት የፍቅር ቀን ቀጠሮ ጥቃት ለደረሰባቸው ለታዳጊ ልጆች እና ለወጣቶች እና ለጓደኞቻቸው እና ለቤተሰብ የተዘጋጀ የ 24/7 ነፃ የስልክ መስመር እና የመስመር ላይ የውይይት አገልግሎት ነው። አገልግሎቶቹ ነፃ እና ሚስጥራዊ ናቸው። ፍቅር መከባበር ነው ለብሔራዊ የቤት ውስጥ ጥቃት ነፃ የስልክ መስመር እና ብሬክ ዘሳይክል ፕሮጀክት አካል ነው።

  • ድህረ ገጽ

    http://www.loveisrespect.org